Alert

Latest News

Stay informed with our latest news, where we share updates and developments on healthcare, medical advancements, and hospital services.

ጤና ሚኒስቴር በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር አካሄደ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበና ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ፣ የአ/አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የሆስፒታሉ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሉጌታ ፣ የጤና ሚኒስቴር መሪ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የፌደራልና ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ማኔጅመንት አባላት፣ የክልልና የከተማ ጤና ቢሮ አመራሮች ፣ የኮ/ቀ ክ/ከ ወረዳ አመራሮች፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ መርሀ-ግብሩን የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ለማህበረሰቡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ተቋማት የእውቅና ሽልማት በመስጠት ካስጀመሩ በኋላ ሁሉም ጤና ተቋማት ከዛሬ ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን እንዲጀምሩ በማሳሰብ ጤና ሚኒስቴርም ለዚህ ተግባር ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገልፀዋል። በመጨረሻም በሆስፒታሉ እየተሰሩ ያሉ ፅዱና ምቹ ጤና ተቋም የመፍጠር ስራና እየተከናወኑ ያሉ ትልልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

Announcements

Coming Soon ...

Videos

Upcoming Events

Coming Soon ...